“ምርኮ” ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ልብወለድ ክፍል

ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ልብወለድ 4

…”ወይኔ ሞቲ!” አለ ሰውዬው ንዴቱ እንደጨመረ ያስታውቃል።”ሃይላችንን በናንተ ላይ መጠቀም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚጨምር ብዬ ነው የተውኩክ እንጂ እዚው ሽባ ነበር የማደርግክ” አለኝ አይኑ ደም ለብሶ።ጥቁር ሰዉ ሲቆጣ እጅግ ያስፈራል።ሰውየው ግን ሲቆጣ ሳጥናኤልን መሰለኝ።

በንዴት የክፍሉን መዝጊያ ከፍቶ መልሶ ወርውሮ ዘግቶት ወጣ።በተወለድኩበት ማህበረሰብ እጅግ የሚጠሉ ጎሳዎች ናቸው የገሊላ ከተማ ነዋሪዎች።ኢቶጵ በምትባል አንድ አለም እየኖሩ እጅግ ተለያይተው የሚኖሩ ጎሳዎች ናቸው።ድንበር ለይተው ጦርነት ከጀመሩ አስር አመታት ገደማ ሆኗቸዋል።ጦርነታቸው ከመድፍ እና ከመትረየስ በላይ በጥንቆላና በመተት በመሆኑ መድፍና መትረየስ ከሚያደርሱት የከፋ ጉዳት ባለፋት አስርት አመታት ደርሷል።እኔ ለመጨረሻ ጊዜ የማስታውሰው እኔን ለዚ ሁሉ እንቆቅልሽ ያበቃኝን ጦርነት ነው።
እዛው ክፍል ውስጥ ወንበር ላይ ታስሬ በሃሳቤ የሆነውን ለማስታወስ ሞከርኩ።
…..አዎ።

ሴት አያቴ ከገሊላዎች በተሰነዘረ ክፉ አስማት ወድቃለች።ጦርነቱ ተፋፍሟል።እኔና አብሮ አደግ ጓደኛዬ ሁለቱ ጓሳዎች የሚያረጉትን ጦርነት ለማየት ተደብቀን ካንድ ዛፍ ስር ነበርን።አዎ አያቴ ስትወድቅ አየኃት።ክው አልኩ ከተደበኩበት ተስፈንጥሬ ልወጣ ስል አብሮአደጌ እጄን ያዘኝ።መነጨኩትና ወደወደቀችው አያቴ በጦርነቱ መሀል እሮጥኩኝ።ዞሬ ሳይ እሱም እየተከተለኝ ነበር። ከኋላዬ ሆኖ ” አዉ ደርሰካል …………ግፋ…….. በርታ ወንድሜ………አምልጥ አምልጥ……እሩጥ” አለኝ።

ከዛሬ 10 አመት በፊት እኔ የዘጠኝ አመት ልጅ እያለው በተደረገ ጦርነት ነበር እናቴና አባቴ የሞቱት ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያሳደገችኝ አያቴ ነበረች።እናትና አባቴ በጎሳችን እጅግ የሚፈሩ ልዩ ኃይል አላቸው የሚባሉ ሰዎች ነበሩ ይህን ኃይላቸውን አያቴ የሰጠቻቸው ሲሆን አያቴም የዋዛ አልነበረችም።በጎሳችን ማንኛውም ልጅ እድሜው 13 ሲሞላ ልዩ ኃይልን ከእናትና ከአባቱ ያገኛል የሚል ስርአት አለ።ነገር ግን እናቴና አባቴ ከሞቱ በኃላ እድሜዬ 13 ሲሞላ አያቴ ያንን ሃይል የመስጠት መብቱ ሲኖራት አያቴ ግን እናትና አባትህን ያጠፉቸውን ሃይል መውረስ የለብህም ብላ በመንደራችን ላለ ገዳም ባደራ ሰጠችኝ።መንፈሳዊዉን አለምና ትምርት እንዳውቅ ብላ።ከዛን ግዜ ጀምሮ እስካሁኑ ጦርነት ጊዜ በነበሩ ጦርነቶች ሰው ሁሉ ደጃፉን ወግቶ በሚደበቅበት ሰአት እኔ ግን በገዳሙ ካወኩት ጓደኛዬ ጋር ተደብቀን በመምጣት ጦርነቱን እመለከት ነበር።

እሮጬ አያቴ ጋር ደረስኩ።ከእግሯ ጫፍ አንስቶ ወደከሰልነት እየተቀየረች ነበር።ታጣጥራለች።የሆነ የሆነ ነገር ደጋግማ ትላለች።በአፋ ስታነበንብ ሰውነቷ ወደቀድሞው ይመለስና መልሶ መጥቆር ይጀምራል።ተንበርክኬ ከትከሻዋ ቀና አረኳት።አይኔን እያየች ጊዜው ደርሷል ይሄንን በል ብላ በጣቷ መሬቱ ላይ ፁሁፍ ፃፈቸልኝ።ፁሁፉ “ኤሽታኦል ናማራዚ” ይላል……..

……”ምንድነው የሆንሽው ውዴ?” አልኩዋት ሴት አያቴ ውድነሽን።”ዝም ብለህ የፃፍኩልህን ስድስት ጊዜ ደጋግመህ በል ብለህ ስትጨርስ አያቶቻችን አሸናፊነትንና ኃይልን ያድሉሃል ከተፈጥሮ በላይ ትሆናለህ።ይህንን ጥበብ ይጠቀሙ የነበሩት የጥንት የኢቶጵ ኃያላን አያቶቻችን ነበሩ።ቃሉን ደጋግመህ ስድስቴ ስትለው ሃይል ሰውነትህን ይሞላዋል።ከዛም ቤተሰቦችህን ያሳጡህን እኒህን ክፋ ጎሳዎች ትደመስስበታለህ።ይህ ጥበብ በራሱ መንገድ ስለሚወስድህ ተከተለው።….” ብላ አይኗን …… ይቀጥላል like ማድረግን አትርሱ !

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*