ምርኮ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ልብወለድ) ክፍል 5

…ብላ አይኗን ከደነች ይህን ስትናገር ሰውነቷን እያከሰለ የነበረው የገሊላውያን ክፋ ጥንቆላ ሰውነቷን እየዋጠው ነበር።

ደጋግሜ ስሟን ተጣራው አያቴ ሞተች።አምርሬ አለቀስኩ።አብሮ አደጌ ትከሻዬን አቅፎኝ አብሮኝ አለቀሰ።ወድያው ንዴትና እልህ ሃዘንና ቁጣ የተቀላቀሉበት ስሜት ሰውነቴን ሞላ።አያቴ ወደፃፈችው ፁሁፍ አይኔ እንባውን ጠርጎ ተመለከተ።ልቤ ደሞ ፈራ።እኔነቴ በቁጡ ስብዕናና በፈርሃ እግዚያቤር መሀል ተወጠረ።የተወጠረው ከረረ።ድንገት ወደሰማይ ቀና አልኩኝ።እግዚያብሄርን በዙፋኑ ፈለኩት።ዙፋኑ ላይ ሆኖ እሱም ባያቴ ሞት እንዳዘነ ገመትኩኝ።

አንገቴን መለስኩኝ።ፁሁፋን ከማለቴ በፊት በልቤ የቅዱስ ሚካኤል ድርሳን ላይ የተፃፈውን ፀሎት አልኩኝ። “አቤቱ እኔም ረቂቃኑን እና ግዙፉኑን ጠላቶቼን ድል እመታ ዘንድ Jack: በትሁት ስብዕና ሁኜ እነዚህን ቃላቶች እፀልያለሁ።እንዲህ እያልኩ….” እያለ ይቀጥላል ፀሎቱ እኔ ግን አያቴ የፃፈችልኝን መድገም ቀጠልኩ።

“ኤሽታኦል ናማራዚ!” አልኩ ድምፄን ከፍ አድርጌ የሆነ ነጎድጓድ ሰማሁ። “ኤሽታኦል ናማራዚ!” ደገምኩት።”ኤሽታኦል ናማራዚ!” ሦስት “ኤሽታኦል ናማራዚ!” አራት “ኤሽታኦል ናማራዚ!” “ኤሽታኦል ናማራዚ!” ድንገት ትልቅ የፍንዳታ ድምፅ በዙርያዬ ተሰማ በቦታው ላይ የነበሩት ጦርነቱን ሲያደርጉ የነበሩት ሁሉም ተዝለፍልፈው ወደቁ ወደጎደኛዬ አየሁ መሬት ላይ ተዘርሯል። ልቤ ስውር ሲል ታወቀኝ።ወደመሬት ወደኩ።…..

አያቴ ያለችው ሆነ ማለት ነው አልኩኝ ለራሴ ከሄድኩበት ሰመመን ነቃሁ።
አሁን በዚ ጥበብ መንገድ ላይ ነኝ? ያ ሃይል ነው የነሱን ሰው ያስመሰለኝ? ምነው አንደበቴን ብትለጉመው ጌታዬ በቀል እኮ የእስራኤል አደለም አልኩኝ በልቦናዬ።ምን አቅብጦኝ ነው ገሊላ እንዳለው እያወኩኝ የኮሬብ ሰው ነኝ ያልኩት።ዳንኤልም ልሁን ሄኖክ አርፌ ዝም አልልም?ደሞስ ከዚ እንቆቅልሽ የሆነቤት እንዴት ነው የማመልጠው?

ወድያው የነሱ ሰው አለመሆኔን ማወቃቸው ልቤን እረበሸኝ።ለካንስ አስረውኛል።ለካ ሞቴን እየደገሱ ነው።የጥቁሩ ሰውዬ እንደዛ ዝቶና ተናዶ መውጣት ከቀድሞው ይልቅ አሁን አስፈራኝ።ምንድነው ማስተዋሌን የሰረቀው አልኩት እራሴን።ደሞም ቤተሰቤን በነጠቁኝ ሰዎች መሀል መሆኔ አስቆጣኝ።ሌላው ቢቀር ሰው ባልገል የቤተሰቦቼን ደም ባልመልስ እራሴን ማዳን ስችል ከዚ እንቆቅልሽ ማምለጥ ስችል ምን ነካኝ? አልኩኝ ለራሴ።ልቤ ተተራመሰ።ፍርሃት ተሰማኝ።ይቀጥላል Like ማድረግን አይርሱ …….

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*