“ምርኮ” ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ልብወለድ ክፍል 6

…በገዳሙ ውስጥ እያለው የተማርኩትን ፀሎት ወደ አምላኬ ፀለይኩ::
“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በስማችሁ ብዙ ተዐምራትን ያደረገ

የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሃገር የተሰበሰቡትን ሰብዐ ነገስታት ደምስሳችሁ እንዳጠፋችኋቸው እኔም ከጠላቶቼ እድን ዘንድ ጠብቁኝ” አልኩኝ በልቤ ወድያው አያቴ ያለችኝ ነገር ትዝ አለኝ።”ቃሉን ደጋግመህ ስድስቴ ስትለው ኃይል ሰውነትህን ይሞላዋል።” ብላኝ እንደነበር ቅድምም እጄ በመስታወቱ ውስጥ ማለፉን በማሰብ የታሰርኩበትን ነገር ለመፍታት መኮርኩ።

ትኩረቴን ለመሰብሰብ ጣርኩኝ።አይኔን ጨፍኜ ሰውነቴን ወጠርኩት።ወድያው እጄም ተፈቶ የታሰርኩበትም ወንበር ተሰብሮ መሬት ወደኩኝ።እጅግ ደስ አለኝ።መሬት ላይ እያለው ድንገት የታሰርኩበት ክፍል በር መንገጫገጭ ጀመረ ሰው እንደመጣ ተረዳሁ።ወድያው መደበቅያ ፈለኩኝ።ነገር ግን ክፍሉ ባዶ ነበር።ተቀምጫ ከነበረበት እና ከተሰበረው ወንበር ውጪ አንዳች የሌለበት ኦና።በሩ እንደመከፈት አለ……

…..በሩ ከፍቶ የሆነ ሰው ገባ።ሰውየው ቀይ ሻሽ ጠምጥሟል በግራ እጁ ጦር ይዟል።ክፍሉ ውስጥ በድንጋጤ ቀጥ ብዬ ቆምኩ።ሰውየው ገብቶ ወደተሰበረው ወንበር አፈጠጠ። ጮክ ብሎ “አንተ ደደብ ሰውየው አምልጧል” ብሎ ዘሎ ወደክፍሉ ገባ።ምን? አልኩኝ ለራሴ።ፊት ለፊቱ ቆሜ እንዴት አያየኝም? የቅድሙ ግዙፍ ጥቁር ሰው እየሮጠ ገባ።አለቀልኝ ብዬ በፍርሀት መራድ ጀመርኩ።ሰውየው ገብቶ ወደተሰበረው ወንበር አፈጠጠ።ቀድሞ የገባው ሰው”የታለ ምርኮኛው?” ብሎ አፈጠጠበት።

“ጌታዬ እዚ ጋር ነበር እኮ ያሰርኩት ደሞ ያለኝን ሁሉ አቅም ተጠቅሜ ነው ያሰርኩት።ያውቃሉ ይሄን ጥበብ ከርሶ ነው የወሰድኩት እንዴት ሊያመልጥ ቻለ?” አለ ቅድም ዝቶብኝ የወጣው ጥቁሩ ሰው።እኔ ክፍሉ ውስጥ ቆምያለው። “ደደብ ነክ” አለ ጌታዬ የተባለው ሰው።”ደደብ ነክ ጨዋታ ነው እንዴ የያዝነው? አንተን ብሎ ባለ አቅም! ይሄ ሰው እንዲች ብሎ አጥሬን ይለፍና ጥቁር ዶሮ ነው አርጌ ነው የማርድክ።

“ብሎ ዝቶበት ወጣ።የተዛተበት ጥቁሩ ሰው ክፍሉ ውስጥ ከኔ ትይዩ ቆሟል።የተሰበረው እንጨት ላይ አፍጧል። እኔ ክፍል ውስጥ ሆኜ እንዳላዩኝ ሳስተውል ላይን እንደተሰወርኩኝ ገባኝና እጅግ ፈራሁ።እንዴት እንደተሰወርኩኝ ስለማላውቅ እንዴት ወደቀድሞዬ እንደመሰመለስ ጨንቆኝ ባለሁበት ቆሜ ቀረው ሰውየውም የተሰበረው ወንበር ላይ እንዳፈጠጠ ነበር።ወድያው እየተበሳጨ በሩን በእግሩ መቶት ወጣ።እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ከአይን ተሰውርያለው።

አሁን ከዚ ክፍል በፍጥነት መውጣት አለብኝ አልኩ ለራሴ ቀስ ብዬ በተከፈተው በር ወጣው።ግራ ቀኜን አማተርኩ።ያ ከውጪ እንደዛ ከማርጀቱ የተነሳ አውሬ እንኳን የማይኖርበት ቤት የሚመስለው ፎቅ ልዩ የሆነ ህንፃ ሆኖ ከታሰርኩበት ቤት ፊት ለፊት ቆሟል።እንዴት እንዲ ሊያደርጉ ቻሉ ብዬ ተደነኩኝ። ለራሴ።ግቢው ውስጥ ድርያ የለበሱ ሴቶች ወደላይ ወደታች ይላሉ።

አንዳንድ ነጭ ቀሚስ የለበሱ አገልጋይ መሰሉኝ በግቢው ውስጥ ይታያሉ። መውጫ ለመፈለግ አስቤ ነገር ግን ማንም እስካላየኝ ድረስ ለምን የጊቢውን አንዳንድ ነገሮች አላይም ብዬ ወሰንኩ።ከየት መጀመር እንዳለብኝ ባላውቅም ፊቴ ወዳለው አንድ ክፍል ቤት አመራው ነጠል ብሎ ስለተሰራ ትኩረቴን ስቦት።ቤቱ በጥቁር እብነበረድ የተሰራ ቤት ነው።መዝጊያውም መስኮቶቹም ከውጭ የሚታየው ገፅታ ሁሉ ጥቁር ነው።ሲታይ ቢያስፈራም መራመዴን ቀጥያለው።

የግቢው ወለል ላይ ትላልቅ ድንጋዬች ተነጥፈዋል።ገባ ወጣ ብለው ለመራመድ ያስቸግራሉ ስራመድ አሁንም አሁንም ያደናቅፉኛል መሬቱን እያየው ብሄድም መደናቀፌ አልቀረም።ልክ ወደቤቱ ስጠጋ አንድ ሹል ድንጋይ አውራ ጣቴን ክፉኛ መታኝ ያደረኩት ነጠላ ጫማ ስለነበር ጣቴ ደማ።አይኔ እያየ ከጣቴ የፈሰሰው ደም ወደመሬት ሲጠልቅ አየሁት።ደሜም መፍሰስ አቆመና ወድያው የቤቱ በር ተከፈተ።

በሩ ሲከፈት የጎላ ድምፅ ነበረው እና በግቢው ውስጥ ሲዘዋወሩ የነበሩት ድርያ የለበሱ አንዕስቶችና ነጫጭ ቀሚስ የለበሱ አገልጋዮች ስራቸውን ትተው ወደተከፈተው በር ቀና አሉ።
የምገባበት ጠፋኝ። ድንገት ከቤቱ ውስጥ የሚያጓራ ድምፅ ሰማው።

ይቀጥላል …..Share & Like ማድረግን አይርሱ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*