“ምርኮ” ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ልብወለድ ክፍል

.እሮጬ አንድ የወደቀ ግንድ ስር ተሸሽጌ ማየት ጀመርኩ።ግቢው ውስጥ የነበሩት አገልጋዬች መተረማመስ ጀመሩ።

በፍጥነትም በግቢው ዙርያ ተሰርተው የነበሩ ክፍሎችን በመክፈት ውስጥ ገብተው ዘጓቸው።ግቢው ባዶ ሆነ።ሁኔታው ግራ አጋብቶኝ ወደተከፈተው ክፍል ፊቴን አዞርኩ።ጭንቅላቴን ለሁለት የሚከፍል ድንጋጤ ተሰማኝ።ከዛ ጥቁር ክፍል ውስጥ ጥቋቁር ክንፎች ያሉት ባለ ቀንዳም ሰው መሳይ ፍጡር ወጣ።እጅግ ግዙፍ ነው።ቁመቱ ከሶስት ሜትር አያንስም።ደረቱ ሰፋፊ ነገር ግን የቆሰሉ ነበሩ።
እጁ ላይ የተበጠሰ ሰንሰለት ይታያል።አንድ ክንፋ እንደተሰበረ ሙሉ ለሙሉ ከክፍሉ ሲወጣ አስተዋልኩ።

ድንገት ከህንፃው ያ ጥቁሩ ሰው ወጣ በእጁ ይዞት የነበረውን አንስተኛ ባሊ መሳይ ነገር ወደ ግዙፉ ሰው ሲወረውረው ውስጡ ያለው ደም መሰይ ነገር ተረጨ ግዙፉ ሰው እጅግ የመረረ ጩኸትን ጮኸ ጩኸቱ ልክ እንደተወጋ ዘንዶ ጩኸት ነበር።ወድያውም ሚዛኑን ስቶ መንገዳገድ ጀመረ።ከዚያም በጉልበቱ ወደቀ።አስሮኝ የነበረው ጥቁሩ ሰውም ከቤቱ ጥግ ተደግፎ የነበረን ጦር አነስቶ በጦሩ ጫፍ ግራ መዳፋን ቀረጠ።ይህን ሁሉ በተጋደመው የዛፍ ግንድ ተከልዬ ሳይ ቆየሁ።ግዙፉ ሰው ከወደቀ በኋላ የሆነው ነገር ስላልገባኝ ከተከለልኩበት የዛፍ ግንድ ወጣው።ሰውየው የመዳፋን ደም የጦርን ጫፍ መቀባት ጀመረ።ተንበርክኮም እራሱን የሳተ የሚመስለው ፍጡር የተደፋበት ደም መሳይ ነገር እንዳፈዘዘው ገባኝ።ነገር ግን ጥቁሩ ሰው ስለምን የእጁን ደም ጦሩን እንደሚቀባ አልገባኝም።ወደነሱ መቅረብ ጀመርኩ።ጦር ወደያዘው ጥቁር ሰው እና ወደተንበረከከው ግዙፍ ሰው ልድርስ አንድ ሃያ እርምጃ ሲቀረኝ ፈዞ የነበረው ግዙፉ ፍጡር ድንገት ቀና ብሎ እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ አየ እና እንደመባነን ብሎ ተነስቶ ቆመ።በድንገትም የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰምቶ ወደ ጥቁር ዘንዶነት ተቀየረ።

ይሄኔ ጦር ይዞ የነበረው ሰው ጦሩን ይዞ ወደዘንዶው ሲንደረደር ዘንዶው በጭራው መቶ እጅግ አርቆ ወረወረው።ከዛም ወደኔ አይቶ “አንተ የርጉም ዘር”አለኝ ዘንዶው።ይሄንን ስሰማ ወደኃላ ሸሸው።ዘንዶው ግን መሬት ለመሬት እየተሳበ ወደኔ መቅረብ ጀመረ።እንዴት ለማንም የማልታይ ሰው ለሱ ታየሁት ደሞስ እኔ የርጉም ዘር? እጅግ ፈራሁ ወደኋላ ስዞር የታየኝ የግቢው የእንጨት አጥር ብቻ ሆነ። ወዴት ብዬ ልሽሽ።ወዴትስ ላምልጥ በማላውቀው መንገድ ለእይታ የተሰወርኩት ሰው ድንገት ለዚ አውሬ ታየሁት።ዘንዶውም የትም ማምለጫ እንደሌለኝ ገብቶት መሰለኝ ረጋ ብሎ እየተሳበ መጣ።እኔም የወደቀውን የእንጨት ግንድ አልፍ አጥሩን ተደግፌ ቆምኩኝ።ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ተመኘው።ድንገት ዘንዶው ልክ የወደቀው ግንድ ጋር ሲደርስ ወደኔ ተወረወረ………ይቀጥላል ….Share & Like ማድረግን አይርሱ

መፅናኛዬ……..ሠዎች ባስተሳሰባቸው ወርደውና ዘቅጠው ኢሞራላዊ የሆነ ነገር ሲናገሩና
ሲያደርጉ ሳይ በጣም እበሳጫለሁ። ታዲያ በዚህች ቅጽበት ቶሎ አዕምሮዬ ላይ ከሚያቃጭሉ የመፅናኛ ሀሳቦች አንዱ ቢኖር ይህ የመጋቢ ሀዲስ እሸቱ
የማስታገሻ (anti pain) ንግግር ነው። ድንቁርና አለመማር እንጂ ትምህርት ቤት አለመሄድ አይደለም፤ ብዙዎች ዶክትረው ሲደነቁሩ፣ ብዙዎችም ትምህርት ቤት ሳይሄዱ ሙሁራን ሲሆኑ አይተናል። ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደም አለ:

የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል። በሌላ ሀገር ትንሽ ወንዝ ካለ መዝናኛ አድርገው ይዝናኑበታል፡፡ እኛ ሀገር ግን ትንሽ ወንዝ ካለ የመለያያ ድንበር አድርገን እንጋጭበታለን፡፡ አለምን የሚያጠፏት ደግሞ ተስፋ የቆረጡ እና ገደብ ያለፈ ተስፋ የሰነቁናቸው፡፡

☞ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለምአየሁ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*