ምርኮ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ልብወለድ ትረካ

ክፍል አንድ ልብ አንጠልጣንና አስተማሪ ትረካ

አንገቴን ቀና አረኩኝ።
ሊወድቅ ያለ ፎቅ ነው ዙርያውን አረንጓዴ የአረም ሀረጎች የበቀሉበት የግንብ አጥር አለው።አጥሩ ውሀ ሰማያዊ የተቀባ ነገር ግን ከፊሉ የዛገ በግምት ቁመቱ ሜትር ከሃያ ገደማ የሆነ የብረት በር አለው።የሚከፈት አይመስልም።
ፎቁን ከላይ እስከ እታች ለማየት ሞከርኩ።ግን አቃተኝ።መላ ሰውነቴ ከጭነት ጋሪዉ ጋር ታስሯል በጀርባዬ ተንጋልዬ በወገቤ እንዲሁም በሁለቱም ትከሻዬ በኩል ያለፈው ገመድ ሁለቱ እግሬን ቀፍድዶኛል።እንደምንም አንገቴን ቀና አረኩኝ።በእንጨት የተሰራ የድሮ የህንፃ አሰራርን የተከተለ አሮጌ ባለ ሶስት ፎቅ ቤት አየሁ።የመስኮቶቹ መስታወቶች ተሰባብረዋል። አብዛኛዎቹ የህንፃው በሮች የተገነጠሉ ናቸው። የበረንዳዎቹ ፍርግርጎች በህንፃው ላይ በበቀሉ ሃረግ መሳይ ነገሮች ተሸፍነዋል።ባጠቃላይ ቤቱ ድቅቅ ያለ አስቀያሜ ቤት መሆኑን አየው። “የት ነው ያለሁት?” አልኩኝ ለራሴ።”ማን ነው ያሰረኝ” “ማነውስ እዚ ያመጣኝ?” “የማን ቤት ነው ይሄ? የምንሳ ጋሪ ነው? እንዴ የት ነኝ?” ማለቅያ እና መላሽ የሌላቸው ብዙ ጥያቄዎች እራሴን ጠየኩ።መልስ የለም።

የታሰርኩበትን ገመድ ልፈታ ታገልኩ ነገር ግን ያልጠበኩት ህመም ሆዴ አካባቢ ተሰማኝ ቀና ብዬ አየሁት…የፈጣሪ ያለህ! ሰውነቴ በደም እርሷል ከሆዴ አሁንም አሁንም ደም ይወጣል ደነገጥኩ አጥወለወለኝ ወደ ላይ ሊለኝም ፈለገ ምን እንደምሆን ጠፋኝ።”እርዱኝ…!” ብዬ ልጮህ ፈለኩ እሱም ተሳነኝ አፌን ስከፍት ጭንቅላቴ አካባቢ ወጋኝ ወድያው ጭንቅላቴ አካባቢም እንደተጎዳው ተረዳው።ቀስ እያሉ አይኖቼ ሊጨፈኑ ሆነ ጉልበቴ ሊከዳኝ ጀመረ።ባይኔ ዙርያ ገባዬን ማየት ጀመርኩ የታሰርኩበት ዘመናዊ የጭነት ጋሪ ከለላ ያለው ነው በሚነዳው ሰው እና እኔ ባለሁበት የጭነት ቦታ መሀል ከለላ አለ የጭነት ጋሪው ፊቱን ከህንፃው ተቃራኒ ሆኖ ቆሞ ስለነበር እኔ በህንፃው ትይዩ ነኝ በአካባቢው ሰው ያለ አይመስልም::

የት እንዳለው ለመረዳት አማራጭ መፈለግ ጀመርኩ ከፎቅ ቤቱ ግንብ ዉጪ ምንም አይታየኝም አይኔ መከደን ጀመረ እንደምንም ገለጥኩት …የፎቁ ግንብ ጎን ስልክ እንጨት አየሁ።ስልክ እንጨቱ ላይ የሆነ ፁሁፍ ተለጥፋል ፁሁፉን መለየት ተሳነኝ አይኔ ተከደነ።…….በጭንቅላቴ ውስጥ ብዙ ጩኸት ይሰማኝ ጀመር።ደጋግሞ ደጋግሞ ግፉ ግፉ ይለኛል አንድ ድምፅ አዉ ደርሷል …………ግፋ…….. በርታ ወንድሜ………አምልጥ አምልጥ……እሩጥ
ድብልቅልቅ ያለ ስሜት የተቀላቀለ ጩኸት።በጭንቅላቴ ውስጥ ይሰማኛል የመኪና ድምፅ የጥይት ተኩስ ድምፅ ተሰማኝ የፍንዳታ ድምፆች አሁንም አሁንም ይሰማል።…….

ደሞም የራሴው ድምፅ ተሰማኝ ግን የማላውቀዉ ቋንቋ ነው
ደግሜ ደግሜ”ኦሽታኦል ናምራስ! ኦሽታኦል ናሚራስ!” እላለው። ድንገት የታሰርኩበት ጋሪ መንቀሳቀስ ጀመረ።
ህመሙ መልሶ አነቃኝ መላ ሰውነቴ የቆሰለ መሰለኝ ህመሙን ልቋቋመው አቃተኝ እንዳልጮኸው ተሳነኝ እንባ ካይኖቼ መውረድ ጀመረ።ከአንገቴ ቀና ስል ጋሪው ፊቱን ወደ ህንፃው መልሶ መሰለኝ እየገባ ነው።ድንገት አንድ ቢጫ ታፔላ ላይ አይኔ አረፈ።…….ክፍል ሁለት ይቀጥላል ሁሌም ፔጃችን ላይ ያገኙታል ሼር ማድረግዎን አይዘንጉ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*