ምርኮ ተከታታይና ልብ አንጠልጣይ የልቦለድ ትረካ ክፍል ሶስት

ልብ እንጠልጣይ ትረካ ክፍል ሶስት

ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ልብወለድ
ክፍል ሶስት….ያበድኩኝ መሰለኝ።”አምላኬ ሆይ እርዳኝ አልኩኝ በልቤ” መስታወቱ ውስጥ ያለው ሰውየም በልቡ እንደዛ ያለ መሰለኝ።እራሴን መምታት ጀመርኩ ህልም መህኑን በማመን እንድነቃ ተስፋ በማድረግ።ሁሉም ነገር ቀፈፈኝ ሌላ ሰው የለበስኩኝ ሆኖ ተሰማኝ ሰውነቴ አቅለሸለሸኝ መሬትና ሰማይ ሊጣበቁ ሲሉ የሚሰማው የህልም አለም ስቃይ አሁን ተሰማኝ።ልክ ተፈጥሮ እንደከዳችኝ አይነት የሆነ ቅጣት ውስጥ እንደገባ ያለ ክፉ ስሜት ልቤን አተረማመሰው።ደሜ ሲቆጣ ልቤ ሲከዳ እኔነቴ ሲሸረሸር ታወቀኝ።

እራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ።ክፍሉ ውስጥ ያለ አንድ ወንበር አንስቼ መስታወቱ ላይ ወረወርኩ።ነገር ግን ያልጠበኩት ነገር ተፈጠረ ወንበሩ ልክ መስታወቱ ጋር ሲደርስ……………. ተሰወረ።የማየውን ማመን ቀላል አልነበረም።በዝግታ ወደ መስታወቱ ተራመድኩ።

ቀስ ብዬ ተጠጋሁት መስታወቱ ፊት ደርሼ እጄን ወደመስታወቱ አስጠጋው የሆነ ልብን የሚሰውር ስሜት ልቤን ተሰማኝ እጄ መስታወቱን አለፈ።በድንገት ያለሁበት ክፍል ተበረገደ እና አንድ ጥቁር እረጅም ሰው ከቅድሙ መብራት ባይኔ ላይ ሲያበራ ከነበረው ሰውጋር ገቡ።እኔም እጄን በፍጥነት መለስኩ።

ሰውየው የተቆጣ ይመስል ነበር ግን ፈገግ አለ።በዛ ጥቁር መልኩ ላይ ፈገግ ሲል ጨለማ የሳቀ መሰለኝ።ወደኔ ተጠጋ በጣም ፈራሁት ሊያንቀኝ የፈለገ መሰለኝ ተጠጋኝ ቀስ ብዬ ወደ ኃላ ተራመድኩ።ፈጠን ፈጠን ብሎ ሲመጣ ልሮጥ ዳዳኝ።ሲራመድ እና ወደኔ ሲጠጋ የሆነ የብዙ ሰዎች ጩኸት የሚመስል ድምፅ ይሰማኝ ነበር።

ሰውየው ተንደርድሮ አቀፈኝ።ክው አልኩ ሞት ያቀፈኝ መሰለኝ።ሰውነቴ የረከሰ መስሎ ታየኝ።”ኤሽታኦል ናማራዚ” አለኝ እንዳቀፈኝ።ቃሉን ስሰማ የሆነ ነገር አደረገኝ ሰውነቴን ወረረኝ ልቤ መምታት ጀመረ “ኤሽታኦል ናማራዚ?……ኤሽታ….” የት ነው የማውቀው ይሄን ቃል ብዬ አሰብኩ በህሊናዬ።ወድያው ትዝ አለኝ ጋሪው ላይ ታስሬ በነበረበት ጊዜ በአይምሮዬ ደጋግሜ እሰማው የነበረው ቃል ነው።

ሰውዬው ጭምቅ አርጎ ለቀቀኝ።ሁለት እርምጃ ተራምዶ እጅ ነሳልኝ።ደነገጥኩ የሆነ ክፋት ልቤን ሲወረኝ ታወቀኝ። ሰውየው ላይ ዝም ብዬ አፈጠጥኩ።ቀና ብሎ አየኝ እና ተነሳ። “ጅማሬውን ፣ ፍፃሜውን ለማየትና ለመፃፍ ጌታችን የመረጠክ ወዳጄ የምትሞት መስሎን ነበር ምስጋና ለጌታችን” አለኝ።

ምንም የሚያወራው አልገባኝም።
“ቆይ ማንናቹ እናንተ እኔስ ማን ነኝ የምኖረው ኮሬም ነበር እንዴት ገሊላ ልመጣ ቻልኩኝ ስሜ ሄኖክ ነው ለምንድነው ዳንኤል የምትሉኝ የምን ጅማሬና ፍፃሜ ነው የምን መመረጥ ነው”አልኩኝ አይኔን እያፈጠጥኩ።
“የሆነ ስህተት አለ ማለት ነው”አለና ጥቁሩ ሰው የሆነ ነገር መድገም ጀመረ ድንገት አንገቴ ሲታነቅ ተሰማኝ ወድያው ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ አለ ተዝለፍልፌ ወለሉ ላይ ወደኩ።………..

የሆነ ከባድ ጥፊ ከሰመመኔ አነቃኝ።ቀና ብዬ አየሁ ጥቁሩ ግዙፉ ሰውዬ ጥቁር ካባ ለብሶ ከፊቴ ቆሟል።”አንተ የእርጉማን ዘር እንዴት መሀላችን ገባህ?” አለኝ እያፈጠጠ።”ማን ናችሁ እናንተ ?” አልኩት ከሰመመኔ እየነቃው።”እንዴት የኮሬም ሰው ሆነህ ደፈርከን? ዳሩ የነዛ ሟርተኞችና መተተኞች ዘር ሆነህ ይህን ባታደርግ ነበር የሚገርመኝ።አሁን ለምንና ምን ይዘህ የኛን ሰው መስለህ እንደመጣህ ንገረኝ።” አለኝ እየጮኸ።
“አስማትና ሟርት በዘር የተሰጠውማ ለክፋት ጌታ ሰራዊቶች ነው።” አልኩት እጄን ለመፍታት እየታገልኩ። ክፍል አራት ይቀጥላል እርስዎ ሼር ማድረግን አይዘንጉ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*