ባንዳ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ትረካ

እያዝናና እዉቀት የሚያስጨብጥ የልቦለድ ትረካ

የጠዋት ፀሀይ በመጋረጃው አልፎ በትንሹ አልጋዋ ላይ አርፏል ዛሬ ከወትሮው በተለየ ተኝታ ስላረፈደች የእህቷ ልጅ ፍላጎት ልትቀሰቅሳት ወደክፍሏ መጣች ስትተኛ በር የመቆለፍ ልምድ የላትም ‹ በር መቆለፍ ምንድን ነው አስተሳሰብ የፈጠረው በሽታ ነው የሂወታችንንም የልባችንንም በር እንደዚህ እንቆልፈው እና አዲስ ነገር ለመቀበል ፣አዲስ ሰው፣አዲስ አስተሳሰብ ወደ ሂወታችን ለማስባት እንቸገራለን › ትላለቸ በዚህ አመለካከቷ ብዙ ጓደኞቿ ይቃወሟታል ‹ቤትሽም ልብሽም ክፍት ሲሆን ለመጎዳት ቅርብ ትሆኛለሽ ድብቅነት ለራስ ነው መተዋወቅ ለመናናቅ በር ይከፍታል በተቻለሽ አቅም ለሰው የማታሳይው የሂወት ክፍል ሊኖርሽ ይገባል › ይሏታል እርሷ ግን ስለሰዎች ተቃውሞ ግድ የላትም እንደምታስበወ በምታምንበት ነገር ለመኖር ትሞክራለች፡፡ ፍላጎት የክፍሉን መጋረጃ ገልጣ ክፍሉ ሙሉ ለሙሉ ብርሀን እንዲያገኝ ስታደርግ የጠዋቷ ፀሀይ ፊቷ ላይ ስላረፈ በርግጋ ተነሳች ፍላጎት የሚሊያርድ የእህቷ ልጅ ናት የአስር አመት ልጅ እና ኢለመንተሪ ተማሪ ናት፡፡


‹‹ሚሊ ትምህርት ቤት እየረፈደ እኮ ነው…›› ሚሊያርድ ከአልጋው ጎን ካለው ኮሞዲኖ ላይ ሰአትዋን አንስታ ተመለከተች እና ‹‹ወይኔ! ደሞ ዛሬ ሰኞ ነው ታክሲ አይገኝም ኤጭ!…አንቺ ቁርስሽን በላሽ ?››በፍጥነት ተነስታ አልጋዋን እያነጠፈች ነው ‹‹ኸረረ አልበላውም አንቺን እየጠበቅኩሽ ነበር›› በአንድ ጎን አልጋውን ማንጠፍ እያገዘቻት ነው ‹‹አንቺ ሂጂ በቃ እኔ ታጥቤ ኢኒፎርም እስክቀይር አንቺ ቁርስሽን ብይ እና እንሄዳለን ›› እየተቻኮለች አልጋውን ማስተካከልዋን ተያያዘችው ‹‹አንቺሳ አትበይም?››እየወጣች በሩን ይዛ ትጠይቃታለች ‹‹ እበላለው ፍልዬ ወይም አንቺ ታጎርሺኛለሽ… በናተሸ ሂጂ ፍጠኚ›› ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አስፓልቱ ዳር ቆመው ብዙ ቢጠብቁም ሰአቱ ተማሪዎች ፣ሰራተኛው እና ወጪ ወራጁ እንቅስቃሴ የሚያበዛበትስለሆነ ታክሲዎች ሁሉ ሞልተው ሲለሚመጡ ለረዥም ሰአት ታክሲ ማግኘት አልቻሉም ነበር በመጨረሻ እረዳቱን ለምና ፍላጎትን ልጅ ስለሆነች አንድ ሰው አቅፏትም ቢሆን እንድትሄድ አደረገች፡፡ አሁንም የታክሲ ግፊያውን ችላ ለማግኘት እየሞከረች ነው እስካሁን አልተሳካላትም፡፡እንደጉድ ውር ውር የሚሉት ባጃጆች ሳይቀሩ በዋናው አስፓልት መንቀሳቀስ ስለተከለከሉ አሁን ውስጥ ለውስጥ ካልሆነ በስተቀር እንደልብ አይገኙም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛ የሚመጣው የሀዋሳ ኑዋሪ እና ጎብኚዎቿ ቁጥር ለኑሮ ውድነቱ የእራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል በእየጊዜው የምታየውን የሰው ብዛት መጨመር እያሰበች እየተገረመች ሳታስበው አንዲት በፍላጎት እድሜ የምትስተካከል እድሜዋ ከአስር የማትዘል ቆንጅዬ ጠይም ልጅ ብቻዋን አስፓልቱን ልትሻገር ሰተት ብላ ስትገባ አየቻት እና መንገዱ ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ ፊቷን ዘወር ስታደርግ አንድ ሚኒ ባስ እየተክለፈለፈ ሲመጣ ተመለከተችው ልጅቷን ልታስቆማት ፈልጋ አንደበቷ አልታዘዝ ሲላት ሁለት እጆቿን እያርገበገበች እየሮጠች ወደ አስፓልቱ ገባች….ግን ልጅቷን ለማዳን እረፍዶ ነበር እያየቻት ስትገጭ ባለችበት ጭንቅላቷን ይዛ ቁጭ አለች ፡፡


የተገጨችው ልጅ ደም አስፓልቱ ላይ ይንፎለፎላል ቁጥር ስፍር የሌለው ሰው ተሰብስቦ የተገጨችውን ህፃን ይመለከታል ግማሹ ያለቅሳል፣ሌላው የአንቡላንስ ስልክ ይጠይቃል ፣አንዳንዱ ከገጫት ሹፌር ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ነው፣አንዳንዱ ደግሞ ምፅ እያለ አልፎ ይሄዳል …ማንም ሰው ደፍሮ የሚነካት አንስቶ ሀኪም ቤት የሚወስዳት ጠፋ ሚሊያርድ በድንጋጤ ባለችበት ቁጭ እንዳለች ሰዎች እየመጡ እያዩዋት ይሄዳሉ አንዲት እናት ‹‹ምነው የኔ ልጅ ተነሽ ደግ ም አይደል ከመንገድ ዳር መቀመጡ ተነሽ›› ብለው ክንድዋን ይዘው አነሱዋት በእጅዋ አንድ አጀንዳ ደብተር እና በጀርባዋ የትምህር ቤት ቦርሳ አዝላለች የተገጨችውን ልጅ ከነዋት የነበሩትን ሰዎች ገፈታትራ ወደ ውስጥ ስትገባ ልጅትዋ ትተነፍሳለች ጭንቅላትዋ ስለተመታ ደም እየፈሰሳት ነው ተጠግታት እራስዋን ቀና አድርጋ ኢኒፎርሟን አሰረችላት አንድ ቀይ መልከመልካም በእርሷ እድሜ የሚስተካከል ወንድ በድንጋጤ ቆሞ እየተመለከታት እንባው በጉንጮቹ ይወርዳሉ ሚሊያርድ ቦርሳዋን እና ይዛው የነበረውን አጀንዳ አስታቅፋው የተገጨችውን ልጅ አንስታ እየተንገዳገደች እየሄደች ‹‹እርዱኝ እርዱኝ እባካችሁ…››ብላ ወደ ቆሙት መኪኖች ስትሄድ የተሰበሰበው ሰው እንደተአምር እያያት መበተን ሲጀምር አንድ ሰው መኪናውን ከፍቶ አስገባት ቦርሳዋን ይዞ የነበረው ልጅ ተከትሏት ገባ ሹፌሩ መኪናውን አየር ላይ እያሥወነጨፈ ቅርብ ወደሚገኝ ሆስፒታል ደረሱ፡፡


የተገጨችውን ልጅ ወደ ድንገተኛ ክፍል ካስገቧት በኋላ ነው ከላይ እስከታች በደም መነከሯን ልብ ብላ ያስተዋለችው አሁንም ግን ልቧ በፍጥነት መምታቷን እና አልፎ አልፎ ሰውነቷ መንቀጥቀጡ አልቀረም ደብተሯን ይዞላት የመጣው ልጅ ‹‹ምነው ደና አይደለሽም ?›› አላት ፊቱ ላይ የእውነት ድንጋጤ እና መረበሽ ይታያል ‹‹ደና….ደና ነኝ የምትተርፍ ይመስልሀል?›› ‹‹አዎ ዶክተሩ ከዚ በላይ ደም እየፈሰሳት ብትቆይ ልትሞት እንደምትችል ነው የተናገረው ልጅቷን ግን ታውቂያታለሽ?›› እንደማታውቃት አንገቷን በመወዝወዝ ነገረችው እና ‹‹አንተስ ታውቃታለክ?›› አለችው ‹‹አዎ የሰፈሬ ልጅ ናት አባቷን ደውዬ ጠርቼዋለው እንዴት እስካሁን እንደቆየ እራሱ ›› ወደ መግቢያው አይኑን ሲልክ ‹‹ያው! እንደውም መጣ ››


‹‹የቱ? ያ! ጋወን የለበሰው ዶክተሩ?›› በመገረም ይሁን ግራ በመጋባት እየተመለከተችው ‹‹አዎ የፍቅር አባት ዶክተር ነው ስነግረው ደንግጦ ከነ ጋወኑ ነው የመጣው ማለት ነው ፍቅር ብቸኛ ልጁ ናት እንዳይኑ ብሌን ነው የሚሳሳላት እይው እንዴት እንደደነገጠ ›› እያለ እያወራት ዶክተሩ አባት አጠገቧ ደረሰ ‹‹እዩኤል ልጄስ? እውነቱን ንገረኝ አለች? ተርፋለች? አሳዩኝ እባካችሁ? የት ነው ያለችው ?›› እያለ መጮህ ጀመረ ክፍል 2 ይቀጥላል ሼር ማድረግ እንዳይረሱ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*