አሳዛኝ ዜና!

በምዕራብ ሸዋ ዞን ጅባት ወረዳ ዛሬ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። በአደጋው 38 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ማኔጅመንት ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ተሰማ ብሩ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ዛሬ ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ላይ ነው። አርባ ሰዎችን አሳፍሮ ከኖኖ ወረዳ በመነሳት ወደ አምቦ ከተማ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3–37423 (ኦሮ) የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው አደጋው ሊደርስ የቻለው።

አደጋው በጅባት ወረዳ ጋሞ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጆሬ በተባላ አካባቢ መድረሱን የገለጹት ኮማንደር ተሰማ፣ በእዚህም የሁለት መምህራን ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ48 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። የመኪናው አሽከርካሪ ለጊዜው መሰወሩንና ክትትል እየተደረገበት መሆኑንም ተናግረዋል።

እንደኮማንደር ተሰማ ገለጻ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው ተሰጥቷል። ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 11 ሰዎችም በአምቦ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ነው የገለጹት። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia