አትንኮሻኮሽ ፡፡ የሂዎት የሞክሮና አስተማሪ ሃሳቦች

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ምርጥ ምክር ከቤተሰብ

ወዳጄ ድፍን ብር እንጂ ዝርዝር ሳንቲም አትሁን አየህ ዝርዝር ሳንቲም ዋጋው ትንሽ ነው መግዛት የሚችለውም ትንሽ ነገር ነው በዛ ላይ ኪስ ውስጥ ሲቀመጥ ይንኮሻኮሻል በህይወት ስትኖርም ልክ እንደ ሳንቲሙ ሁሉ ትንንሽ ዝርዝር ሠዎች ያጋጥሙሀል እነዚህ ሠዎች አንተ ስትሰራ ይንኮሻኮሻሉ አንተ ግን አይግረምህ ሁሌም ትንሽ ነገር መጮህ እንጂ መስራት አይችልምና ፡፡ 

በህይወትህ ዝርዝር ሠዎች ሲገጥሙህ ድፍን ብር ሆነህ አስገርማቸው አየህ ድፍን ብር ድምፅ የለውም ዋጋውም ከፍተኛ ነው ትልልቅ ነገር መግዛትም ይችላል አንተም ዋጋህ ከፍተኛ ይሁን ከፍ ስትል ወዳጅህም ፈላጊህም ይበዛልና ፡፡


ፌስ ቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም !! ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ። በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ።
: ሼር ለወዳጆዏ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*