ዐዲስ አበባችን ዛሬ ምን አዲስ ነገር አስተናገደች …

መስቀል አደበባይ በአዲስ አበባ ስታዲዮም

ሰልፉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታዎች ለአስተዳደሩ አንዱን እንዲፈቀድ ካልሆነ ለውይይት በር እንዲከፍት በማለት ምርጫ ቀርቦለታል፡፡ ለእሁድ.በመስቀል አደበባባይ በተጠራው ሰላማዊ ሰልፉ ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርጫ ቢቀርብለትም እስካሁኑ ድረስ መልስ ለመስጠት አልፈለገም፡፡ ከአዲስ አበባ ፖሊስና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ጋር አዘጋጅ ኮሚቴ ተነጋግሮ መግባባት ላይ ሲደርሱ የሰልፉ ቀናት አጥሯል አስረዝሙ የጥበቃ ሃይል እንጨምር ባሉት መሰረት ወቅታዊ ችግሮችን ከግምት በማስገባት ቀኑን በማስረዘም በትላንትናዉ ሰኞ ዕለት #ለታህሳስ 14 ሰላማዊ ሰልፉ መዞሩን በመጥቀስ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በደብዳቤ አዘጋጅ ኮሚቴው በማሳወቅ ቅድመ ዝግጅት ቢጀምርም እስካሁን ድረስ ከከተማው አስተዳደር ምንም አይነት ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ቀደም ሲል የተጠየቀው ጥያቄ የከተማዉ አስተዳደር ለማግዝ የተጠራ ሰልፍ ነው በማለት ከፍተኛ ፍርሃት እንደነበር ከአንዳንድ ሁኔታዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡ በከንቲባዉ ጽ/ቤት በኩል ም ከንቲባ ታከለ ኡማ አነጋግራቸዋለሁ በማለት ቀጠሮ ከመስጠት ውጭ በጉዳዩ ዙሪያ ከኮሚቴውን ጋር ተቀራርቦ ለመነጋገር ፍቃደኛ አለመሆናቸው ታይተዋል፡፡ አዲስ አበቤ ቀና እንዳትል የሚሸረብ ጨዋታ ይግባህ፡፡

በአምቦ ዩኒቨርስቲ የወሊሶ ካምፓስ የተማሪዎች ዉይይት መጨረሻ ለይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶር ታደሰ ቀነኣ የተጠቀሙት አስደናቂ ስልት። አሥር የኦሮሞ ተማሪዎች ፣ አሥር የአማራ ተማሪዎች እንዲሁም አሥር ተማሪዎች ከሌሎች ብሔረሰቦች ወደፊት እንድወጡ ጠየቋቸው ። ተማሪዎቹም በተጠየቁት መልኩ ወጡ ። ተቀላቅለው እንዲሰለፉ ተጠየቁ ። እንደተጠየቁም አደረጉት። አንድ ጥያቄ ለተዳሚዎች አቀረቡ ከተሰለፉት ታማሪዎች ማን ኦሮሞ ፣ ማን አማራ ፣ ማን ትግሬ ፣ ማን ጉራጌ ወዘተ እንደሆነ ለይቶ የሚነግረን ብሎ ጠየቁ ። ሁሉም ዝም ዝም አሉ ። አንድ ናይጄሪያዊ ወይም ቻይና ብቀላቀል መለያት የቅተናል ወይ ብሎ ጠየቁ ። ሁሉም በአንድ ድምፅ አያቅተንም ብሎ መለሱ ። ስለዚህ ካለብን ልዩነቶች በጭንቅላታችን የሚንፈጥራቸዉ ልዩነቶች ስለሚበልጡ አንድነታችንን እናጉለ አሉ። ተማሪዎቹም ተቃቅፈው በአንድነት ወደ መመገቢያ ቦታ ሄዶ ምሳቸዉን በሉ ።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*