የማይሽር ጠባሳ ተከታታይ የልቦለድ ትረካ ክፍል 1

በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

ታሪኬ የሚጀምረው ገና የሁለት ወር ህፃን እያለው እናቴ ለእንጀራ እናቴና ለ አባቴ እኔና ታላቅ ወንድሜን ጥላን የጠፋች እለት ነበር አዎ ገና የሁለት ወር ጨቅላ እያለው በእንጀራ እናቴ እጅ እድገቴን ጀመርኩ በርግጥ አባቴ ልጆቹን ወዳጅ ስለነበር እንጀራ እናታችን እኛን ለመጉዳት መንገድ አልነበራትም
ውልደቴም እድገቴም በ ወለጋ ነቀምቴ ነበር አባታችን የራሱ ገቢ ነበረው እናታችን ጥላን ብጠፋም ታላቅ ወንድሜ እጅግ ይወደኝ ስለነበር አንድም ቀን እንድከፋ አይፈልግም ይበልጥ ከአባቴና እንጀራ እናቴ ወንድሜ ይጠብቀኝ ነበር ከዛ ባሻገር የእርሻ ቦታም ነበረን አባቴ ከመደበኛ ስራው ባሻገር የእርሻ ቦታውን ዘወትር የመጎብኘት ልምድ ነበረው ግን ከለታት በአንዱ ቀን ከስራ መልስ ወደ እርሻ ቦታ የመሄድ ልምድ ስላለው እንደ ልማዱ ወደ እርሻ ቦታ አመራ ነገር ግን የዛሬው የእርሻ ቦታ ጉብኝቱ የህይወቴን ሁለተኛ ምእራፍ ገና በለጋነቴ በጨቅላነቴ እንድጀምር አረጋት.

አባቴ በእባብ ተነድፎ በሰዎች እርዳታ እቤት በገባ በ3 ቀን በህይወት አጣነው ነገር ግን አባቴ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ለእንጀራ እናቴ ቃል አስገባት “ልጆቼን በምድር ሰጥቼሻለው በሰማይ እቀበልሻለው ” ይህ ቃል በልጅነት አእምሮዬ ተፅፎ ቀረ በወቅቱ ወንድሜ እንጀራ እናቴ ስታለቅስ እሱም አብሮ እያለቀሰ ነበር እኔ ግን ልጅነቴ ምኑም እንዲገባኝ አላደረገም ነበር እንጀራ እናቴ ከሌላ የወለደቻቸውና በትዳር ላይ የሚገኙ ሁለት ሴት ልጆች ነበርዋት አባቴ ከሞተ በኃላ ግን እንጀራ እናቴም ጤንነት ስለማይሰማት ልጆችዋ ወሰድዋት ።ይህ 3ኛው ምእራፍ የኔና የወንድሜ ነበር እኔና እኔን በ6 አመት ልዩነት ያለን ወንድሜ ብቻችንን ኦና ቤት ታቅፈን ቀረን ።

የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት ቤት ውስጥ ኑሮአችንን መግፋት ጀመርን ወንድሜ ከኔ የተሻለ ስለነበር ቀን ቀን ምግብ ፍለጋ ሄዶ ማታ ለሱ ሳይበላ ለኔ ይዞ ይመጣ ነበር በዚህ ሁኔታ ግን ስላልቻልን ጎረቤት ተጠጋን እሱ በእረኝነት እኔ ደግሞ እንደ ልጅነት ልንኖርበት አዎ የተጠጋናቸው ሰዎች ያላቸው ስለነበሩ ወንድሜ ለኔ መስዋት በመሆን ደሞዙ የኔ በሳላም በደስታ እዛ ቤት መኖር ብቻ ነበር እንዲ እንዲ እያልን ለአንድ አመት ኖርን በመሀል የምንኖርባቸው ሰዎች አዲስ አበባ በትዳር የምትኖር ትልቅ ልጅ ነበራቸው በተሰብዋን ለመጠየቅ በምትመጣበት ሰአት እኔ አይንዋ ውስጥ ገባው ስለ እኔ ጠየቀች ሁሉንም ተረዳች አዘነችም ወስዳም እንደምታስተምረኝ ቃል ገባች ወንድሜም በገጠመኝ እድል ደስተኛ ስለነበር ሳያቅማማ ፈቀደ እኔም ልጅነቴ እንዳለ ያገኘውት እድል አስደስቶኝ ስለ እኔ መሰዋት የሚሆነውን ወንድሜን ትቼ ወደ አዲስ አበባ ገሰገስኩ…… ይቀጥላል ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉት ።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*