የቤቲ እዉነተኛ ታሪክ ክፍል አንድ ይህ እውነተኛ ታሪክ

ይህ እውነተኛ ታሪክ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ብዙ ቀናት ስለ ቤተልሔም ይተርካል።

ታሪኩ ላይ የስም ብቻ ለውጥ ተደርጎበት ቤቲ ድንግልናዋን ካጣችበት ቀን ጀምሮ እስከ አሁን ያለችበት ሁኔታ በሰፊው ይተርካል። ሙሉ ስሙዋ ቤተልሄም ገዛኸኝ ይባላል።የተወለደችው ክፍለ ሀገር ቢሆንም ያደገችው አዲስአበባ ውስጥ ነው።ቀይና ቆንጅየ ልጅ ናት።የመጀመሪያ ፍቅር የያዛት university ነበር። ድንግልናዋን ያጣችው ግን ባልታሰበ አጋጣሚ ሰርግ ቤት ነው።ስለሱ በክፍል 2የምነግራቹ ይሆናል።አሁን ስለመጀመሪያ ፍቅርሲይዛት ልንገራቹ።ስትማር የነበረው ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነበር።አንድ እዩኤል ከሚባል ዱርየ ልጅ ነበር ያው ፍቅር የማይጥልበት ቦታ አይታወቅም። ስታየዉ ትሸሻለች…አይከተላትም… ባጋጣሚ ከተገጣጠሙ “ሰላም!” ብቻ ብሏት ያልፋል… ይህ ደግሞ የሚያቀራርብ እንጂ ወዴትም የሚያስሸሽ ነገር አይደለም… ለሷም ግራ የሚገባት ይኸዉ ነዉ። “ቆይ ግን ምን ሆኛለሁ!” በማለት ራሷንስትጠይቅ ሽሽት ላይ ያለዉ ልቧ ፍርሃትን እንጂ ምንም አይነግራትም…እንደፈራች ይነግራታል… ይህ ፍርሃት እየበቀለ ሔዶ ስለ እዩኤል እያሰበች ዉላ ታድራለች…ጓደኞቿ መቀየሯን ነግረዋታል… እነሱ ራሳቸዉ መቀየራቸዉን ነዉ የምታዉቀዉ…በሷ አለም ዉስጥ የተጨመረ አንድ ይህ ነዉ የማይሉት ፍርሃት ነዉ…ዩኒቨርስቲዉ ዉስጥ አብራቸዉእየሔደች ከሩቅ ስታየዉ መርበትበቷን እንዳያዉቁባት እየተጠነቀቀች ሰርቃ ታየዉና ምድር ዋጥ ስልቅጥ ባደረገቻት እየተመኘች ትሸሻለች… ይህ ሁኔታዋ እያደር ሲብስ ግልጽ እየወጣ በመሔዱ ጓደኞቿ ዶርም ዉስጥ አስቀምጠዉ ምን እንደሆነች ጠየቋት… ነገረቻቸዉ…

“እኮ ይሄ ዱርየው?” አንዷ፣ “እንዴ ልጅቷ አበደችንዴ!” ሌላዋ፣ “ባክሽ አወዳደቅሺን አሳምሪ!” ደግሞ ሌላዋ። ይህ አባባላቸዉ ለጊዜዉ ለቸገራትነገር መፍትሔ አላመጣም። የባሰ አስጨነቋት። የባሰ እዩኤል አሳዘናት። ጓደኞቿ ገፉት። ተቀየመቻቸዉ። ………… አንድ ቀን (ሲኒየሯ ስለሆነ) የጥናት እና የምርምር ስራ በዝቶባት አንድ ክፍል ዉስጥ ተቀምጣ ትላልቅ ወረቀቶች ላይ ስታሰማምር አያት። ማገዝ እንደሚገባዉ ተረዳና “ምን ላግዝ!?” አላት። የያዘችዉን ማስመሪያ እና እርሳስ ለቀቀችዉ። የድምጹ መለስለስ። ይዞት የመጣዉ የአየር መቅለል። የፊቱ ፈገግታ። የሆነ አስታራቂ ድባብ። ሰዉን ከአለም ጋር የሚያስታርቅ ዉብ እጅግ ዉብ ድባብ። ……………… “አንተ!” አለችዉ። ሳቀላት። ሼር ማድረግ አይዘንጉ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*