የአንድነት ፓርክ ዛሬ ይመረቃል አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራው የአንድነት ፓርክ በዛሬው እለት ይመረቃል።

በዛሬው እለት የሚመረወቅ የአንድነት ፓርክ የመደመር እሳቤ ማሳያ ነው ያለው የጠቅላይ
ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፥ ያለፉትን ታሪካዊና ማህበራዊ እሴቶቻችን እየዘከርንና ለመጪው
ትውልድ እያጎለበትን እንሂድ ሲል ጋብዟል።

አንድነት ፓርክ ለጋራ ግባችን በአንድነት ቆመን የፍፃሜውን ምዕራፍ ዘመን ተሻጋሪ በሆነ
የሕብረት አቅም ማጠናቀቅ የመቻላችን ተምሳሌትም ብሏል ጽህፈት ቤቱ።
በዛሬው እለት የሚመረቀው የአንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች
ለጎብኚዎች ክፍት የሚደረግ ይሆናል።
በዚህም መሰረት በነገው እለት የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በቤተ
መንግስት ግቢ የተሰራውን የአንድነት ፓርክ የሚጎበኙ ይሆናል።
ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ በእድሜ ታላላቅ ዜጎች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ቤተ መንግስቱን
ይጎበኛሉ።
ከስኞ ማለትም ከጥቅምት 3 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር እንዲሁም በቪአይፒ
(VIP) 1 ሺህ ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት እንደሚችልም ተገልጿል።