ጨፍጫፊ ማለት በአራዳ ቋንቋ ታላቅ ውሸታም እንደማለት ነው፡፡አዲስ አበባችን ደግሞ በርካታ መድረክ ላይ ያልወጡ ቀልደኞች ባለቤት ነች ከእነርሱ መካከል የእንግሊዝ ኤምባሲውን ጋሽ አበቤ እና የስድስት ኪሎው ውብሸት ዋነኞቹ ናቸው።

ሸገር ላይ ተወልዶ ያደገ አበቤን አልያም ውበሸትን ያላወቀ ሠው ይኖራል ብዬ አላስብም አበቤን ባያውቅ ውብሸትን ያውቃል ውብሸት ባያውቅ አበቤን ያውቃል ሁለቱንም ባያውቅ የእነርሱን ጭፍጨፋዎች ወይም የማይታመኑ ውሸቶች ሰምቶ ያልሳቀ የአዲስ አበባ ልጅ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ታላላቅ ጨፍጫፊዎች እነማን ናቸው ሠው በምናብ የፈጠራቸው ወይስ እውነተኛ? ጋሽ አበቤ አበቤ ከአራት ኪሎ እስከ ኮተቤ ከእንግሊዝ ኤምባሲ እስከ ቦሌ ድረስ ገናና ድንቅ ጨፍጫፊ ናቸው ሠው አንድ ውሸት ሲፈጥር እንኳን አበቤ እንዲህ አሉ እያለ ያወራል፡፡ አበቤ በተለምዶ እንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ (አሁን በህይወት ይኑሩ አይኑሩ እርግጠኛ አይደለሁም) ታላቅ ጨዋታ አዋቂ በአራዳ ቋንቋ ጨፍጫፊ ናቸው አሁን አሁን አካባቢው አበቤ ሱቅ እየተባለ ይጠራል፡፡ የእርሳቸው ቀልድ ከሚኖሩበት እንግሊዝ ኤምባሲ ተነስቶ መላ አዲስ አበባን ያስቅ እንደነበር አስታውሳለው፡፡ የእርሳቸው ቀልድ በብዛት እጅግ ሠቅጣጭ ውሸት የተቀላቀለበት እንደሆነ ቀልዳቸውን የሠማ ያስታውሰዋል፡፡

ለምሳሌ በአንድ ወቅት ነው አሉ ጋሽ አበቤ በአንድ ወቅት በግ ነጋዴነት እሰራ ነበር ነገር ግን የበግ ዋጋ ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ከመርከሡ የተነሳ ምን ይሻለኛል ብዬ ስጨነቅ አንዱ በግ ነጋዴ ጋሽ አበቤ ኬንያ የበግ ዋጋ ጥሩ ነው ስለዚህ ለምን ኬንያ ሄደን አንሸጥም ሲለኝ ተስማምቼ ጉዞ ወደ ኬንያ ጀመርን ነገር ግን ሞያሌ ስንደርስ የያዝነው ምግብ ስላለቀ ምን ይሻላል ብዬ ብጠይቅ ከያዝናቸው በጎች መካከል አንዱን አርደን እንብላ የሚል ሐሳብ ጓደኛዬ አቀረበ ነገር ግን አንድ በግ አርደን በልተን እንደማንጨርሰው|ሳቅ መላ ፈጠርኩኝ እና በጉን አረድነው የቻልነውን ያህል ከበላን በኋላ የተረፈውን ስጋ ድቅቅ አድርጌ ከከተፍኩኝ በኋላ እዛው መሬት

ላይ ዘራሁት ኬንያ ደርሰን የያዝናቸውን በጎች ሸጠን ስንመለስ እነዛ የዘራኋቸው የደቀቁ ስጋዎች በቅለው ግልገል ሆነው ስለጠበቁን እነርሱን እየነዳን አዲስ አበባ ገባን እላቹሐለው>> ይህ ነው ጋሽ አበቤ
ታላቁ የመዲናይቱ ጨፍጫፊ እና የበርካታ ቀልዶች ባለቤት በአሁን ሠዐት አበቤ ሱቅ የሚባል እንግሊዝ አካባቢ እንዳለ አውቃለው በተረፈ ስለእርሳቸው ከሠማው ቆየው

ውብሸት ውብሸት ሌላው እና ድንቅ ውሸታም ነው መኖሪያው ስድስት ኪሎ 17 ቀበሌ ሲሆን የእርሱ ቀልዶች ግን ከተማይቱን ሲያስቁ ኖረው አሁንም በማሳቅ ላይ ናቸው፡፡ውብሸት አሁንም በህይወት ያለ ሲሆን በወጣትነቱ ሯጭ ነበር አሁን ላይ መብራት ኃይል የመብራት ቆጣሪ አንባቢ ሆኖ እንደሚሠራ አንድ ወዳጄ ነግሮኛል፡፡ ከውብሸት ቀልዶች መካከል እንደ አበቤ ከኬንያ ጋር የተያያዘውን ላጫውታቹህ፡፡<<በአንድ ወቅት ሯጭ እያለው ልምምድ እየሠረው ነበር እናም በጠዋት ተነስቼ ከሰፈሬ ከስድስት ኪሎ ጀምሬ አንገቴን አቀርቅሬ ስሮጥ ሜዳ ገደሉን ተራራ ሸለቆውን እያቆራረጥኩኝ ስሮጥ ስሮጥ ከበርካታ ሠዐት በኋላ ቀና ስል ከፊት ለፊቴ <<wel come to Kenya>> የሚል ፅሁፍ አነበብኩኝ።>> እኔም የእነርሱን ቀልድ እያሠማሁኝ አድጌ የዘንድሮ ኮሜድያኖች ቀልድ ሼር ያድርጉ