“የፌስቡክ ገፁን ልሽጥልሽ ጭምር ሲለኝ ነበር”–አርቲስት ሜሮን ጌትነት በስሟ ተከፍቶ 260,000 ተከታይ ስላፈራው የሀሰት የፌስቡክ ገፅ ከተናገረችው! ሰሞኑን መነጋገርያ በነበረው በገጣሚ እና ተዋናይዋ ስም ስለተከፈተው ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ ዙርያ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከሜሮን ጌትነት ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።  ሜሮን ጌትነት ስለጉዳዩ ይህን ብላለች፦

“የሚገርመው ዘመድ እና ጓደኞቼ ጭምር ይህ ገፅ የኔ ይመስላቸው ነበር። እኔ ግን ለበርካታ ግዜያት የኔ ትክክለኛ ገፅ #እንዳልሆነ በኢንስታግራም አካውንቴ ስገልፅ ነበር። ሌላው የሚገርመው የዚህ 260,000 ተከታይ ያለው ገፅ ባለቤት ገፁን ልሽጥልሽ ስለዚህ እንደራደር ሲለኝ ነበር። ዝም ስለው ቆይቶም አብረን አድሚን ሆነን ስራ እንስራበት ሲለኝ ነበር። የዚህ ሁሉ ንግግር ስክሪንሾት አለኝ። ለማንኛውም አሁን ለፌስቡክ ሪፖርት አድርጌው እንዲዘጋ አደርገዋለሁ። ትክክለኛው አካውንቴ ይህ ነው: